የሞባይል መተግበሪያዎች
ከመስመር ውጭ/ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ ነጻ፣ ባለብዙ ቋንቋ መተግበሪያዎች ስብስብ። በተጠቃሚ ማኅበረሰቦች የተፈተኑ፣ የሄስፔሪያን መተግበሪያዎች ሚስጢራዊነትን ያስቀድማሉ።
ከመስመር ውጭ/ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ ነጻ፣ ባለብዙ ቋንቋ መተግበሪያዎች ስብስብ። በተጠቃሚ ማኅበረሰቦች የተፈተኑ፣ የሄስፔሪያን መተግበሪያዎች ሚስጢራዊነትን ያስቀድማሉ።
ወሲብ መቼ ማድረግ፣ መቼ መጸነስ እና ልጅ መውለድ እንዳለብን ለራሳችን ስንወስን ጤናማ እንሆናለን። የሄስፔሪያን ለአጠቃቀም ምቹ እና ባለብዙ ቋንቋ መተግበሪያዎች የታመኑ የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃዎችን እና አጋዥ መሳሪያዎችን ያካትታሉ። አንዴ ካወረዷቸው በኋላ እነዚህ መተግበሪያዎች ያለበይነመረብ ግንኙነት ወይም የውሂብ ዕቅድ/የዳታ ጥቅል ይሠራሉ። ለራስዎ፣ ለወዳጆችዎ እና ለማኅበረሰብዎ ጤናማ ውጤቶችን የሚያረጋግጡ ውሳኔዎችን ለማድረግ ይጠቀሙባቸው።
ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ
ስለ ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ትክክለኛ፣ የተሟላ እና ቅደም ተከተሉን የጠበቀ መረጃ ያግኙ። የተለያዩ ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ዘዴዎችን ያወዳድሩ፣ የእርግዝና ጊዜ ማስያውን ይጠቀሙ፣ እንዲሁም ለጥያቄዎችዎ መልስ ያግኙ ብሎም በተደጋጋሚ የሚነሱ ስጋቶችን በብዛት ከሚጠየቁ ጥያቄዎች ሰፊ ዝርዝር ላይ በማጠቀስ ይመልሱ። ግለሰቦች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የመብት ተሟጋቾች አውርደው እንዲጠቀሙበት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ መጠኑ አንሶ (ከ40ሜባ በታች) እና የተጠቃሚን መረጃ ሚስጢራዊነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተዘጋጀ ነው።
የቋንቋዎች ዝርዝር
• Afaan Oromoo
• Amharic
• English
• Spanish
• French
• Igbo
• Kinyarwanda
• Kiswahili
• Luganda
• Portuguese
• Yoruba
በማንኛውም ጊዜ በ11ኡም ቋንቋዎች መካከል ይቀይሩ።
Family Planning app
ታካሚዎችን ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች፣ የአካባቢ መሪዎች፣ እና ለአቻ አስተማሪዎች የተዘጋጀው ይህ መተግበሪያ፣ በሥነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚደረጉ ንግግሮችን ለመደገፍ ግልጽ በሆኑ ፎቶዎች እና ምሳሌዎች፣ ለመረዳት ቀላል በሆነ መረጃ እና እርስበርስ በተገናኙ መሳሪያዎች የተሞላ ነው። የቤተሰብ ዕቅድ ስለእያንዳንዱ ዘዴ አጠቃቀም፣ እርግዝናን ስለከላከል ዓቅሙ፣ በቀላሉ በምስጢር መያዝ ስለሚቻልበት መንገድ የሚገልጹ፣ እናየጎንዮሽ ጉዳቶችን ጨምሮ ለምክር አስፈላጊ የሆኑ ርእሶችን ይሸፍናል።
የቋንቋዎች ዝርዝር
• Afaan Oromoo
• Amharic
• English
• Spanish
• French
• Kinyarwanda
• Kiswahili
• Luganda
• Portuguese
ሁሉንም 9 ቋንቋዎች እንደምርጫዎ ይቀያይሩ።
Safe pregnancy and birth app
Safe Pregnancy and Birth provides accurate, easy-to-understand information on pregnancy, birth, and care after birth. Clear illustrations and plain language make this award-winning app practical and user-friendly for community health workers, midwives, and individuals and their families. Free and small to download, this app works offline without a data plan.
Language choices in the Safe Pregnancy and Birth app: English, Español. Change between both languages at any time.