የቤተሰብ ዕቅድ መተግበሪያ
ከመስመር ውጭ የሚሰራ ነጻ ባለብዙ ቋንቋ መተግበሪያ።
በመስክ የተሞከረው በማህበረሰቦች፣ የሄስፔሪያን መተግበሪያዎች ግላዊነትን ያስቀድማሉ።
ታካሚዎችን ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች፣ ለአካባቢ መሪዎች እና ለአቻ አስተማሪዎች የተዘጋጀው ይህ መተግበሪያ፣ በሥነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችን ለመደገፍ ግልጽ በሆኑ ፎቶዎች እና ምሳሌዎች፣ ለመረዳት ቀላል በሆነ መረጃ እና እርስበርስ በተገናኙ መሳሪያዎች የተሞላ ነው። የቤተሰብ ዕቅድ ስለእያንዳንዱ ዘዴ አጠቃቀም፣ እርግዝናን ስለመከላከል ዓቅሙ፣ በቀላሉ በምስጢር መያዝ ስለሚቻልበት መንገድ የሚገልጹ፣ እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ጨምሮ ለምክር አስፈላጊ የሆኑ ርእሶችን ይሸፍናል።
በቤተሰብ ዕቅድ መተግበሪያው የተካተተ:
-
የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች – ስለ ማገጃ፣ ባሕርያዊ፣ የሆርሞን እና ዘላቂ ዘዴዎች እና ስለ እያንዳንዳቸው ውጤታማነት፣ ጥቅሞች እና ጉዳቶች መረጃ
-
ዘዴ መምረጫ – ሰዎች እንደምርጫቸው፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው እና የጤና ሁኔታቸው ይበልጥ የሚስማሟቸውን የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች እንዲያገኙ የሚረዳ መሳርያ
-
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች – ስለ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለሚነሡ ብዙ አጠቃላይ ጥያቄዎች፣ እና ኮንዶም እንደገና መጠቀም ስለመቻል እና ከወለዱ፣ ጽንስ ከጨነገፈባቸው ወይም ጽንስ ካቋረጡ በኋላ እያንዳንዱን ዘዴ መቼ መጠቀም መጀመር እንችላለን እንደሚሉት ላሉ የተለመዱ ስጋቶች ምላሽ ይሰጣል
-
ጠቃሚ ምክሮች እና መስተጋብራዊ የምክክር ምሳሌዎች – የማማከር ችሎታዎን ያሻሽሉሎታል፣ የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃን በምቾት ለመወያየት፣ እንዲሁም የተለያዩ ታሪኮች ያሏቸውን እና ከተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የመጡ ሰዎችን መደገፍ ያስችሉዎታል