ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ
ከመስመር ውጭ የሚሰራ ነጻ ባለብዙ ቋንቋ መተግበሪያ።
በመስክ የተሞከረው በማህበረሰቦች፣ የሄስፔሪያን መተግበሪያዎች ግላዊነትን ያስቀድማሉ።
እርግዝናን ስለማቋረጥ ትክክለኛ፣ ሰፊ እና ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ መረጃ ያግኙ። በቀላል ቋንቋ የተጻፈ እና ወቀሳ የሌለበት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ የጽንስ ማቋረጥ እገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ወይም የሚሰጡ ሰዎችን ሊረዳ ይችላል። በነጻ ያውርዱ ወይም እዚህ በድረ-ገጻችን ላይ ያለውን መተግበሪያ ይጠቀሙ።
በአስተማማኝ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ ውስጥ ያሉ የቋንቋ ምርጫዎች፦ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ፈረንሣይኛ፣ ኢግቦ፣ ኪንያርዋንዳ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሉጋንዳ፣ ፖርቹጊዝ እና ዮሩባ። በማንኛውም ጊዜ በ11ኡም ቋንቋዎች መካከል ይቀይሩ።
ይህ መተግበሪያ ማንኛውንም የግል መረጃ አይሰበስብም!

Watch the video and download the app!
መተግበሪያውን በመስመር/በኢንተርኔት ላይ ይጠቀሙ
በመፈለጊያዎት ውስጥ ያለውን መተግበሪያ ሳያወርዱ ይጠቀሙበት።
በመፈለጊያዎት ውስጥ ያለውን መተግበሪያ ሳያወርዱ ይጠቀሙበት።
ደህንነቱ የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ ውስጥ
-
በእንክብል፣ በመዋጥ፣ በማሟሟት እና በመጥረግ ስለሚደረጉ ደህንነታቸው የተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ዘዴዎች ግልጽ እና ሙሉ መግለጫዎችን ያግኙ
-
በተለያዩ ሳምንታት ውስጥ በመድኃኒት ጽንስ ለማቋረጥ (ከሚፌፕሪስቶን ጋር ወይም ያለ እሱ) የሚወሰደውን ሚሶፕሮስቶል ክኒን በትክክኛ መጠን ስለመጠቀም እና ስላወሳሰዱ መረጃ ያግኙ
-
በጽንስ ማቋረጥ ወቅት እና በኋላ ምን እንደሚጠበቅ እና የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ከታዩ እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚቻል ይወቁ
-
የጽንስ ማቋረጥን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማካሄድ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ነገሮችን ዝርዝር በመጠቀም ያቅዱ፤ ለአካልዎ እና ለስሜቶችዎ እንዴት እንደሚጠነቀቁ ምክረ ሐሳቦችን ያግኙ
-
“ለአገርዎ” የሚለው ገጽ በመጎብኘት ሊያግዙ የሚችሉ ድርጅቶች እና ተዛማጅ የሕግ ደንቦች የሚያሳዮ ማስፈንጠሪያዎችን ያግኙ
-
ለጥያቄዎችዎ መልስ ያግኙ ብሎም በተደጋጋሚ የሚነሱ ስጋቶችን በብዛት ከሚጠየቁ ጥያቄዎች ሰፊ ዝርዝር ላይ በማጠቀስ ይመልሱ።
-
መተግበሪያውን በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ፣ በፖርቹጊዝ ወይም በፈረንሳይኛ ሲጠቀሙ በድምጽ ማንበብ አማራጭ አማካይነት መረጃውን ያዳምጡ
ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ የተጠቃሚ መረጃ ሚሲጢራዊነትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ነው። ከ40 ሜባ በታች የሆነውን ይህን መተግበሪያ ካወረዱት፣ ያለ የውሂብ ዕቅድ/ዳታ ጥቅል ወይም ያለ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ በነጻ ይሰራሎታል፡፡ በስልክዎ/በኮምፒውተሮ ላይ፣ በመተግበሪያው ምልክት ሥር ያለው ስም “SA” ብቻ ያሳያል።
ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ መተግበሪያ ፈጣን መመሪያ
Print the guide
Instructions for quick assembly
Click images below to enlarge.